SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

ለድንገተኛ የልብ ህመም አጋላጭ ነገሮች ምንድናቸዉ?

04,August 2121

ለድንገተኛ የልብ ህመም አጋላጭ ነገሮች ምንድናቸዉ?

ክፍል ሁለት( heart attack)

የተወሰኑ ምክንያቶች ስብ በደም ቧንቧዎች ዉስጥ ባልተፈለግ መንገድ እንዲጠራቀምና በሰውነትዎ ውስጥ የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ለልብ ድንገተኛ ህመም አስተዋፅኦ ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ፦

·         እድሜ፦   ዕድሜያቸው ከ45 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ55 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሴቶች  ከወጣት ወንዶችና ሴቶች ይልቅ ለድንገተኛ የልብ ድካም የመጋልጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

·         ሲጋራ ማጨስ፦ ሲጋራ ያሚያጨሱም ይሁን ሲጋራ ባያጨሱም ለረጅም ጊዜ ለሲጋራ ጭስ የሚጋልጡ ሰዎች ለድንገተኛ የልብ ችግር ተጋላጭነታቸዉ ከፍተኛ ነዉ።

·         ከፍተኛ የደም ግፊት፦ ከፍ ያለ የደም ግፊት ያላቸዉ ሰዎች በጊዜ ሂደት ወደ ልባቸዉ ደም በሚያደርሰዉ የደም ቅዳዎቻቸዉ ላይ ጉዳት ያደርሳል። ከደም ግፊቱ በተጨማሪ ዉፍረት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮልና የስኳር  ህመም ካልዎ ችግሩን ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል።

·         ከፍተኛ የደም የስብ መጠን፦ ከፍተኛ የሆነ የደም የኮሌስትሮል፣ትራይግላይሴራይድና ሎዉ ዴንሲቲ ሊፖ ፕሮቲን የስብ መጠን መኖር የደም ቧንቧ ጥበት እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

  • ዉፍረት፦ ከመጠን በላይ መወፈር ከከፍተኛ የደም ኮሌስትሮል መጠን ፣ ከፍ ካለ ትሪግሊሴሪይድ መጠን ፣ ከደም ግፊት እና ከስኳር በሽታ ጋር የተቆራኘ ነው።
  • የስኳር ህመም፦ የስኳር ህመም ለልብ ድንገተኛ ህመም ያጋልጣል።
  • በቤተሰብ ዉስጥ መሰል የልብ ችግር መኖር፦ ወንድሞችና እህቶችዎ ፣ ወላጆች ወይም አያቶችዎ ቀደም ብሎ የልብ ድካም አጋጥሟቸዉ ከነበር (ለወንዶች ዕድሜ በ55 ዓመትና ለሴቶች በ65 ዓመት) እርስዎ ለድንገተኛ የልብ ህመም ተጋላጭነትዎ ከፍትኛ ነዉ።
  • ጭንቀት፦
  • አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ፦ እንደ ኮኬይን ወይም አምፌታሚን ያሉ የሚያነቃቁ መድኃኒቶችን መጠቀም የልብ የደም ቅዳዎች( coronary arteries) እንዲኮማተሩ (spasm) ስለሚያደርግ ለድንገተኛ የልብ ህመምን ሊያስነሳ ይችላል።
  • ሜታቦሊክ ሲንድሮም፦ ይህ ሲንድሮም የሚከሰተዉ ከመጠን በላይ ውፍረት ፣ የደም ግፊት እና ከፍተኛ የደም ስኳር መጠን ሲኖርዎ ነው። ሜታቦሊክ ሲንድሮም ያላቸዉ ሰዎች ችግሩ ከሌላችዉ ጋር ሲነፃፀሩ ለድንገተኛ የልብ ችግር የመያዝ እድልን በእጥፍ ይጨምራል።

ድንገተኛ የልብ ህመምን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች

ቀደም ብሎ ድንገተኛ የልብ ህመም ቢኖሮትም  ባይኖሮትም ድንገተኛ የልብ ህመም ችግር  እንዳይከሰት ለመከላከል የሚረዱ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘግየት የለቦትም፡፡ ድንገተኛ የልብ ድካምን ለመከላከክል የሚረዱ መንግዶች ዉስጥ

1. መድሃኒቶችን መዉሰድ፦ችግሩ ዳግም እንዳይከሰትና የተጎዳዉ ልብ እራሱን ጠግኖ በአግባቡ እንዲሰራ መድሃኒቶችን በአግባቡ መዉሰድ

2. የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድራግ፦ ድንገተኛ የልብ እንዳይከሰት  ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን ማድረግ በጣም ውጤታማው መንገድ ነው። ከነዚህም ዉስጥ፦

•           ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ

•           ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ ወይም እያጨሱ ከሆነ ማቆም

•           የደም ግፊትዎን መቆጣጠር

•           ጤናማና የተስተካከለ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ማድረግ

•           በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

•           ጭንቀትን መቀነስ

•           ስኳር ህመም ካለዎ የስኳር ቁጥጥርዎን በደንብ ማድረግ ወይም ስኳር እንዳይዝዎ መከላከል

•           ኮለስትሮልን ጨምሮ ሌሎች የሰዉነት ስቦችን መቀነስ/መቆጣጠር ናቸዉ።


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: