SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የአፍንጫ አለርጂ

20,August 2121

የአፍንጫ አለርጂ

ክፍል አንድ

ወቅቱ ክረምትና ቃዝቃዛ ነዉ። የአፍንጫ መዝረብረብ፣ የአይንና አፍንጫ ማሳከክ አንዲሁም ማስነጠስና የአፍንጫ መታፈን ወይም መዘጋት ስሜት አለዎ? እንግዲያዉስ  ይህ የአለርጂ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባልሙያዎን ያማክሩ።

የአፍንጫ አለርጂ ጉንፋን መሳይ የህመም ምልክቶች ያሉት የህመም አይነት ነዉ። ከመደበኛ ጉንፋን የሚለየዉ ግን እንደ ጉንፋን በቫይረስ ምክንያት የሚከሰት አይደለም። አለርጂ የሚከሰተዉ በቤትና ከቤት ዉጪ ባሉ አለርጂን ሊቀሰቅሱ በሚችሉ ነገሮች ነዉ። አለርጂ በስራ ቦታ፣ በትምህርት አፈፃፀምና በህይወትዎ ላይ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ኑሮዎን ሊያመሰቃቅል ይችላል።

የህመም ምልክቶች

·         የአፍንጫ መዝረብረብ፣ ማሳከክና መታፈን

·         የአይን መቅላት፣ ማሳከክና እንባ መኖር

·         ማስነጠስ

·         ሳል

·         የአፍንጫ፣ ትናጋና ጉሮሮ ማሳከክ ውይም መብላት

·         የአይን የታችኛዉ ቆብ ስር ማበጥና መጥቆር

·         ድካም

·         ከሰርን ወደላንቃ የሚወጣ ፈሳሽ መኖር  

የፍንጫ አለርጂ የህመም ምልክቶች በዓመት ዉስጥ በተወሰኑ ጊዜያት ወይም ወቅቶች ሊባባስ ይችላል። ህመሙን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ነግሮች ዉስጥ

·         የዛፍ፣ የአበባና የሳር የአበባቸዉ ርጋፊ( ፖለን)

·         አቧራ

·         የድመት ሽንትና ካካ ሽታ፣ በረሮና አይጥ ያለበት ቦታ የሚነሳ ሽታ

·         በቤት ዉስጥ ይሁን ከቤት ዉጪ ከፈንገስና ሻጋታ የሚነሳ ሽታ ናቸዉ።

ለአፍንጫ አለርጂ መከሰት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች

·         አስምና ሌሎች አለርጂዎች መኖር

·         የቆዳ አለርጂ ካለዎ

·         በቤተሰብ ዉስጥ( እናት፣ አባት፣ እህትና ወንድም) አስምና ሌሎች አለርጂዎች መኖር

·         ሁልጊዜ ለአለርጂዎች በሚያጋልጥዎ አካባቢ ውስጥ መኖር ወይም መሥራት

·         እናቱ ሲጋራ የምታጨስ ከሆነ በተለይ በህፃኑ የመጀመሪያ ዓመት ዕድሜዉ ወቅት


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: