SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ

31,July 2121

በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ

ወቅቱ ክረምትና ብርድ ነዉ። ብርዱን ለመቀነስም ይሁን ሌሎች የቤት ዉስጥ ስራዎችን ለመከወን ከሰል አቀጣጠሎ መጠቀም በሀገራችን  የተለመደ ነዉ። ከሰል፣ ኩበትም ይሁን ሌሎች በነዳጅ የሚሰሩ ምድጃዎች ጭስ አላቸዉ። የሚሰሩት ቦታ ጠባብ አሊያም በቂ የአየር ዝዉዉር በሌለዉ ክፍል ዉስጥ ከሆነ ጭሱ በክፍሉ ዉስጥ ይጠራቀምና ያፍነናል ለካርቦን ሞኖኦክሳይድ መርዛማ ጋዝም ያጋልጠናል። ለመሆኑ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ ምንድነዉ? ለምን አይነት ችግር ያጋልጣል? እንዴትስ መከላከልና ማከም ይቻላል?

በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ (Carbon monoxide poisoning)

ካርቦንሞኖኦክሳይድ - የማይታይ ገዳይ!!!!

ክፍል አንድ

አንድ ሰዉ በካርቦን ሞኖኦክሳይድ የሚመረዘዉ በደሙ ዉስጥ ያለዉ የካርቦን ሞኖኦክሳይድ መጠን ከፍተኛ ሲሆን ነዉ። በምንተነፍሰዉ ከባቢ አየር ዉስጥ የካርቦን ሞኖኦክሳይድ መጠን ከፍተኛ ከሆነ  ሰዉነትዎ በቀይ ደም ሴሎች ዉስጥ ያለዉን ኦክሲጂን በካርቦን ሞኖኦክሳይድ እንዲተካ ያደርጋል። ይህ ደግሞ ለሰዉነት አካላት መጎዳትና ችግሩ በቶሎ ካልተቀረፈ ለህልፈተ-ህይወት ይዳርጋል።

ካርቦን ሞኖኦክሳይድ ሰዉን ሊገድል የሚችል ከለር፣ ጣዕምና ሽታ የለሽ የጋዝ አይነት ነዉ። የሚመረተዉም ከሰል፣ እንጨት፣ ቤንዚን፣ ፐሮፔነና ሌሎች የሀይል ምንጮች በሚቃጠሉበት ወቅት ነዉ። አየር በደንብ በማይዘዋወርበትና ጠባብ ወይም ዝግ ክፍሎች ዉስጥ ከሰልን ጨምሮ ሌሎች ከላይ የተዘረዘሩትን ነገሮች ማቀጣጠል የካርቦን ሞኖኦክሳይድ ጭስ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ሊጠራቀም ወይም ሊጨምር ስለሚችል በዚህ ቦታ ሆነዉ ይህን ጋዝ የሚምጉ ወይም የሚተነፍሱ ሰዎችንና እንስሳት በካርቦንሞኖኦክሳይድ  ሊመረዙ ይችላሉ።

በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ የህመም ምልክቶች

በጣም በብዛት ከሚታዩ የህመም ምልክቶች ዉስጥ

·         የራስ ምታት

·         መደካከም

·         ማዞር/ማጥወልወል

·         ማቅለሽለሽና ማስታወክ

·         የደረት ህመም

·         የትንፋሽ ማጠር

·         ብዥ ማለት

·         መቀባዠርና እራስን መሳት ናቸዉ።

በተለይ በተኙበት ወይም መጠጥ ወስደዉ ሰክርዉ ከሆነ በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ አደገኛ ነዉ። ሰዎች የማይስተካከል ወይም የማይመለስ የአንጎል መጎዳት አሊያም ማንም ሳያያቸዉና ሳይደርስላችዉ እንዲሁም ችግሩ ሳይታወቅ በተኙበት ሞተው ሊገኙ ይችላሉ።

ለካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ በይበልጥ ተጋላጭ እነማናቸዉ

ሁሉም ሰዉ ለካርቦን ሞኖኦክሳይድ መርዝ ተጋላጭ ነዉ። ሕፃናት ፣ አዛውንቶች ፣ ሥር የሰደደ የልብ በሽታ ፣ የደም ማነስ ወይም የመተንፈስ ችግር ያለባቸው ሰዎች በካርቦን ሞኖኦክሳይድ የመመረዝና የህመም ምልክቶች የማሳየት እድላቸዉ ከፍተኛ ነው።


You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: