SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የልብ ድካም

25,July 2121

የልብ ድካም

የልብ ድካም ምልክት ከታየብዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ። ከሚከተሉት ዉስጥ የትኛዉንም የህመም ምልክት ከታየብዎ በአፋጣኝ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ
የደረት ላይ ህመም
ከፍተኛ የሰዉነት መድከምና ራስን መሳት
ከትንፋሽ እጥረት ፣ ከደረት ህመም ወይም ራስን ከመሳት ጋር ተያይዞ ፈጣን ወይም መደበኛ ያልሆነና የተዛባ የልብ ምት
ድንገተኛ ፣ ከባድ የትንፋሽ እጥረትና አረፋማና ቀላ ያለ አክታ ያለዉ ሳል
ምንም እንኳ እነዚህ ምልክቶች ከልብ ድካም ጋር ተያይዞ የሚመጡ ቢሆንም ተመሳሳይ የህመም ምልክት ያላቸዉ ለህልፈተ-ህይወት ሊዳርጉ የሚችሉ የልብና የሳንባ ችግሮች አሉ።
የልብ ድካም ኖሮት የህመም ምልክቶቹ በድንገት እየተባባሱ ከመጡ አሊያም አዲስ የህመም ምልክት ከመጣ የነበረዉ የልብ ድካም እየተባባሰ መቷል ወይም እየወሰዱት ያልዉ መድሃኒት በትክክል እየሰራ አለመሆኑን ያሳያል።
የልብ ድካም እንዴት ይከሰታል
ከሚከተሉት መካከል ማናቸውም ሁኔታዎች ልብዎን ሊጎዱ ወይም ሊያዳክሙ እንዲሁም የልብ ድካም ሊያስከትሉ ይችላል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ እርስዎ ሳያውቁት ሊኖሩ ይችላሉ፦
የልብ የደም ቅዳ የደም ቧንቧ ህመምና ድንገትኛ የልብ ህመም( Coronary artery disease and heart attack)፥- የልብ የደም ቅዳ የደም ቧንቧ በሽታ በጣም የተለመደ የልብ ህመም ዓይነትና በጣም ከተለመዱ የልብ ድካም መንስኤዎች ዉስጥ ዋነኛዉ ነው። ይህ ችግር የሚከሰተዉ በደም ቅዳዎች ዉስጥ ስብ በሚጠራቀምባትና ወደ ልብ የሚሄድዉን የደም ዝዉዉር በሚቀንስበት ወቅት ሲሆን ይህ ደግሞ ለድንገተኛ የልብ ህመም ይዳርጋል።
ከፍተኛ የደም ግፊት፦ የደም ግፊትዎ ከፍተኛ ከሆነ ደምዎ በሰውነትዎ ውስጥ ሁሉ እንዲሰራጭ ለማድረግ ልብዎ ከሚገባው በላይ ጠንክራ መሥራት አለባት። ከጊዜ በኋላ ይህ ተጨማሪ የልብዎ ጥረት የልብዎን ጡንቻ በጣም ጠንካራ ወይም በጣም ደካማ ሊያደርግ ይችላል።
በትክክል የማይሰሩ የልብ ቫልቮች፦ የልብዎ ቫልቮች ደም በልብዎ ውስጥ በተገቢው አቅጣጫ እንዲፈስ ወይም እንዲንቀሳቀስ ያደርጋሉ። በትክክል የማይሰሩ የልብ ቫልቮች ልብዎን የበለጠ እንድትሠራ ሊያስገድድ ይችላል ፤ ይህም ከጊዜ በኋላ ልብን ሊያዳክም ይችላል።
የልብ ጡንቻዎች መጎዳት( ካርዲዮማዮፓቲይ)፦ ይህ የልብ ጡንቻዎች መጎዳት በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ የሚችል ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ህመሞች፣ ኢንፌክሽኖች፣ ከመጠን ያለፈ የአልኮሆል መጠጥ፣ ለኬሞቴራፒ ህክምና እንዲሁም እንደ ኮኬይን ያሉ የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን ይችላል። የዘረመል ምክንያቶችም እንዲሁ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ
የልብ ጡንቻ መቆጣት( ማዮካርዳይትስ)፦ ማዮካርዳይትስ የልብ ጡንቻ መቆጣት ሲሆን በብዛት ኮቪድን ጨምሮ በቫይራሶች አማካይነት ይከሰታል። ይህ በግራ በኩል የልብ ድካም እንዲከሰት ያደርጋል።
ሲወለዱ ጀምሮ ተፈጥሮያዊ የሆነ የልብ ችግር (congenital heart defects)፦ በፅንስ ወቅት የልብ ጡንቻና ቫልቮች ላይ የአፈጣጠር ችግር ከነበረ የልብ ድካም ችግር እንዲከሰት ያደርጋል።
ያልተስተካከለ የልብ ምት፦ ያልተለመዱ የልብ ምቶች ለልብዎ በፍጥነት እንድትመታ በማድረግ ልብዎን ለተጨማሪ ሥራ በመዳረግ ጫና ሊፈጥር ይችላል
ሌሎች ችግሮች፦ እንደ ስኳር፣ ኤች አይቪ የታይሮይድ ሆርሞን መጨመር ዉይም መቀነስ፣ የብረት ማዕድን በልብ ጡንቻዎች ዉስጥ መጠራቀም( ሄሞሲድሮሲስ) ወይም ፕሮቲን መጠራቀም አሚሎይዶሲስ ለልብ ድካም መከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.

You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: