SHASHE MEDIUM CLINIC

Call us for any question

0468103905 / 0993788686

Shashemenne Jamaican Sefer, Behind NOC Gas Station

Ethiopia

Office Hour: 08:00am - 05:30pm

info@shasheclinic.com

የልብ ድካም

24,July 2121

የልብ ድካም

የልብ ድካም የሚከሰተዉ ልብ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉ ሌሎች አካላትን ለመደገፍ ደም እና ኦክስጅንን በበቂ መጠን መርጨት በማትችልበት ጊዜ ነዉ። የልብ ድካም ሲባል ልብ ሰራዋን ሙሉ በሙሉ አቁማለች ለማለት ሳይሆን ልብ ደም መርጨት ባለባት መጠን እየረጨች አይደለም ለማለት ነው።
ሰውነትዎ ኦክስጅንንና በምግብ ንጥረነገሮች የበለፀገ ደምን ወደ ሰውነት ሴሎች ለማድረስ በልብ ምት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ህዋሳቱ በትክክል ሲመገቡ ወይም ምግብ ሲደርሳቸዉ ሰውነት በመደበኛነት ስራዉን ይሰራል ፡፡ በልብ ድካም ወቅት የተዳከመች ልብ ስለሚኖር ደም ለሴሎች በበቂ መጠን ማድረስ አትችልም፡፡ ይህ የሰዉነት ድካምና የትንፋሽ እጥረት ያስከትላል እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ላይ ሳል ሊከሰት ይችላል። በተጨማሪም እንደ መራመድ ፣ ደረጃ መውጣት ወይም ትንሽ እቃዎችን መሸከም ያሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡
የህመም ምልክቶች
የልብ ህመም ለረጅም ጊዜ የቆየና ስር የሰደደ አሊያም በድንገት የሚከሰት ሊሆን ይችላል።
የህመም ምልክቶቹ
የትንፋሽ ማጥር፦ ይህ እንደ ህመሙ ደረጃ ቢለያይም ሲንቀሳቀሱ፣ ስራ ሲሰሩ ወይም ደረጃ ሲወጡ ሊታይ ይችላል። ህመሙ ከፍ ያለ ከሆነ ደግም ዕረፍት በሚያደርጉበትም ወቅት ሊታይ ይችላል።
ድካምና የሰዉነት መዛል
እብጠት፦ የእግር፣ የሆድና የፊት እብጠት
የልብ ምት ፍጥነት መጨመር ወይም ያልተስተካከለ መሆን
እንቅስቃሴ የማድረግ አቅም መቀነስ
የማያቋርጥ ሳል፦ ሳሉ ደም የተቀላቀለበት ወይም ነጭ አክታ ያለዉ ሊሆን
ይችላል
የሆድ እብጠት
የምግብ ፍላጎት መቀነስና ማቅለሽለሽ
የትኩረት መቀነስና ንቁ አለመሆን
በድንገት በከፍተኛ ሁኔታ ትንፋሸ ማጠርና ደም የቀላቀለ አረፋማ አክታ
መከሰት
የደረት ላይ ህመምና የመሳሰሉት ናቸው።
አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.

You May Also Like

24 Hour Emergency

Open round the clock for conve-nience, quick and easy access

Complate Lab Services

Cost-efficient, comprehensive and clinical laboratory services

Medical Professionals

Qualified and certified physicians for qulity medical care

EMERGENCY CALL: